የተጀመሩ ፕሮጀክቶች እንዲጠናቀቁ እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት ገቢን አሟጦ መሰብሰብ አማራጭ የሌለዉ ጉዳይ ነዉ

የተጀመሩ ፕሮጀክቶች እንዲጠናቀቁ እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት ገቢን አሟጦ መሰብሰብ አማራጭ የሌለዉ ጉዳይ ነዉ

የተጀመሩ ፕሮጀክቶች እንዲጠናቀቁ እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት ገቢን አሟጦ መሰብሰብ አማራጭ የሌለዉ ጉዳይ ነዉ አሉ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ ።
‎ከንቲባ ጥራቱ በየነ ይህን ያሉት ዛሬ በከተማዋ ላለፉት 100 ቀናት በንቅናቄ ተጀምሮ የቆየውን የዕቅድ አፈፃፀም በአመራር ደረጃ በተገመገመበት መድረክ ላይ ነው።
‎በመድረኩ ላይ ከንቲባ ጥራቱ በየነ በተቀናጀ የአመራር ጥረትና ስርዓት እንዲሁም የህብረተሰብ ተሳትፎ በመታገዝ የከተማችንን ከፍታ ወደ ላቀ ደረጃ ያደረሰ የኮሪደር ልማት ስራችንን ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ በተገኙበት ማስመረቅ መቻሉን እንደ ትልቅ ስኬት አንስተዋል።
‎ይህ ስኬታማ ጉዞዓችን ለነገ መጠነሰፊ የልማት ውጥናችን ተነሳሽነትን የሚሰጠን እንጂ በተገኘው ውጤት ረክተን የምንቀመጥ እንደማያደርገን በማመን ይበልጥ በላቀ ቁርጠኝነት የህዝባችንን እና የከተማችንን ቁጭት እውን ለማድረግ መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።
‎እንደ ከተማ የተጀመሩ ፕሮጀክቶች እንዲጠናቀቁ እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት ገቢን አሟጦ መሰብሰብ አማራጭ የሌለዉ ጉዳይ እንደሆነ አመራሩ በትኩረት ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
‎የህዝባችንን ኑሮ ለማሻሻል ያለንን ዕድል እና አቅም አሟጦ መጠቀም ይገባል ያሉት ከንቲባው ለዚህም በ100 ቀናት ዕቅዳችን ላይ በጉድለት የተለዩ አንኳር ስራዎችን ለቅመን ከዳር ለማድረስ መስራት እንደሚገባም አሳስበዋል።
‎የሀዋሳ ከተማን ከፍታ የሚያሳድገው የኮሪደር ልማት ስራችንን በዘላቂነት የልማቱ አካል ለማድረግ መላው አመራር፣ ነዋሪውና የፀጥታ መዋቅሩ ከማንኛውም ህገወጥ አጠቃቀምና አያያዝ እንዲታደገው በባለቤትነት ሊሰራ ይገባልም ሲሉ ከንቲባዉ ተናግረዋል።
‎የሀዋሳ ከተማ ህዝብ ግንኙነት መረጃ እንደሚያሳየው ፡ከንቲባ ጥራቱ በቅርብ መጋቢት 5 እና 6 በክልላችን ዋና ከተማ ሀዋሳ በድምቀት የሚከበረውን የፊቼ ጫምባላላ በዓልን በአመራሩ ከዝግጅት ምዕራፍ ጀምሮ የተሰጠውን ሀላፊነት በመወጣት ለበዓሉ ድምቀት የበኩሉን እንዲወጣም ቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
‎የሀዋሳ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ማራዶና ዘለቀ በበኩላቸው ከተማዋ የሀገር መከላከያ ሰራዊት የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ 65ኛ አመት የምስረታ በዓልን በስኬት ያለ ምንም እንከን በማከናወን እምርታ ማስመዝገብ ችላለች ብለዋል።
‎ይህ በእንዲህ እንዳለም በላቀ የአመራር መናበብና የተልዕኮ ቅብብሎሽ እንዲሁም የአመራር ስርዓት የከተማዋን ውበት ወደላቀ ደረጃ ከፍ ያደረገ የኮሪደር ልማት ስራን ማስመረቅ መቻሉንም እንደ ስኬት አንስተዋል አቶ ማራዶና።
‎እንደ ከተማ የተሰሩ መሰረተ ልማቶችን መጠበቅ እንዲሁም መንከባከብ ሁሉም ባለድርሻ አካላትም ማህበረሰቡም በእኔነት ስሜት መንከባከብ እንደሚገባ በማንሳት በተጨማሪም የጽዳት እና የድች ጠረጋ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አቶ ማራዶና አሳስበዋል።


አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ