ለይርጋለም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እድሳትና ማስፋፊያ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር 271 ሚሊዮን ብር ተሰበሰበ።

ለይርጋለም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እድሳትና ማስፋፊያ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር 271 ሚሊዮን ብር ተሰበሰበ።

ለይርጋለም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እድሳትና ማስፋፊያ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር 271 ሚሊዮን ብር ተሰብስቧል።
የቀድሞዉ የት/ቤቱ ተማሪዎች ሃሳብ አመንጪነትና አነሳሽነት ለት/ቤቱ እድሳትና ማስፋፊያ የመሠረት ድንጋይ በሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ተቀምጧል ።
ገቢ የማሰባሰቡ መረሃ ግብሩ ከሁሉም የአገሪቱ አከባቢ በተለያየ የሥራ ዘርፍ ተሠማርተው እና በመንግሥት የሥራ ኃላፊነት ላይ የሚገኙ የቀድሞ ተማሪዎች፣ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ፣ የንግዱ ማሕበረሰብ ፣ የክልሉ የተለያዩ አከባቢ ነዋሪዎች እንዲሁም መምህራንና ተማሪዎች በተገኙበት ነው የተከናወነው ።
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተደድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ፤ ለይርጋዓለም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት አዲስ ለሚገነቡት ሁለት ሕንፃዎች የክልሉ መንግሥት 200 ሚሊዮን ብር ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል ።
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በየነ ባራሳ በበኩላቸውጨ ፤ ትምህርት ትዉልድ የሚቀረጽበት ማዕከል በመሆኑ ለትምህርት ልማት ሥራ መተባበር የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት መሆኑን አስገንዝበዋል ።


አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ