በሀዋሳ ከተማ የጎዳና ላይ ኢፍጣር መርሃ ግብር ተካሄደ

በሀዋሳ ከተማ የጎዳና ላይ ኢፍጣር መርሃ ግብር ተካሄደ

በሀዋሳ ከተማ፣ የረመዳን ወርን መንፈሳዊ እሴት የሚያንጸባርቅ የጎዳና ላይ ኢፍጣር መርሃ ግብር ተካህዷል።
ዘንድሮ "የነጃሺ ሀገር" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው ይህ መርሃ ግብር፣ የሙስሊም ማህበረሰብ አንድነትና መተሳሰብን የሚያጎለብት መድረክ ሆኗል።
የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ በመርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት፣ ይህ መርሃ ግብር አቅመ ደካማ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችንም ማሳተፉ አብሮነትንና ፍቅርን በማጉጎልበት ረገድ ያለው ሚና የጎላ መሆኑን ገልጸዋል።
የሀይማኖት አባቶችም በበኩላቸው የእስልምና እምነት ትምህርት እንደሚያስረዳው፣ ረመዳን የመደጋገፍ፣ የመረዳዳት እና የበጎ ሥራ ወር በመሆኑ ይህንን ለምዕመኑ ለማስተማር እንዲህ ያለ መርሀግብር አስተዋፅኦ የጎላ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በዚህ ሥነ ሥርዓት ላይ በርካታ የእምነቱ ተከታዮች ተሰብስበው፣ ፆማቸውን በጋራ የሚፈቱበት እና የሶላት ጸሎትን በአንድነት የሚፈጽሙበት ድባብ ተፈጥሯል።
ተሳታፊዎች እንደገለጹት፣ መርሃ ግብሩ በማህበረሰቡ ዘንድ ነባር የሆነውን የመተሳሰብ፣ የመረዳዳት እና የመከባበር እሴት ይበልጥ እንዲጠናከር አስተዋጽኦ አድርጓል ብለዋል።


አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ