ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአዘርባጃን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ጀመሩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአዘርባጃን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ጀመሩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአዘርባጃን ሪፐብሊክ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት መጀመራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል።
የኢትዮጵያ እና አዘርባጃን ግንኙነት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየጠነከረ መጥቷል፤ ለዚህም ጉልህ ማሳያው በጠንካራ ትብብር የቀጠለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ጎልቶ ይታያል።
ይኅው ላቅ ያለው የሁለቱ ሀገራት ቅርርብን ተከትሎ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአዘርባጃን ሪፐብሊክ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት መጀመራቸውን ነው ጽሕፈት ቤቱ ያስታወቀው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ጋር ዛሬ ረፋድ ላይ በባኩ ሄዳር አሊዬቭ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሰዋል።
በዚህኛው ጉብኝት የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን የላቀ እና ትርጉም ያለው ደረጃ እንደሚያደርስ ይጠበቃል ሲል ጽሕፈት ቤቱ ገልጿል።


አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ