የሀዲያ ብሔር የዘመን መለወጫ “ያሆዴ” በዓል በሀዋሳ ከተማ በድምቀት ተከበረ

የሀዲያ ብሔር የዘመን መለወጫ “ያሆዴ” በዓል በሀዋሳ ከተማ በድምቀት ተከበረ
የሀዲያ ብሔር የዘመን መለወጫ “ያሆዴ” በዓል በሀዋሳ ከተማ በድምቀት ተከበረ
********
​ ሀዋሳ፣ መስከረም 07፣ 2019 (ኤስቢሲ)
​ የሀዲያ ብሔር ተወላጆች የዘመን መለወጫ “ያሆዴ” በዓል በሲዳማ ክልል ርዕሰ መዲና ሀዋሳ ከተማ ከነዋሪዎች ጋር በጋራ በድምቀት ተከብሯል።
​በሲዳማ ባህል አዳራሽ በተካሄደው በዚህ ሥነ-ሥርዓት፣ የበዓሉ መክፈቻ በሀዲያ ሀገር አባቶችና የባህል ሽማግሌዎች ምርቃት የተከናወነ ሲሆን፣ ፕሮግራሙ በባህላዊ ዜማዎችና ውዝዋዜዎች ታጅቦ ተካሂዷል።
​በመድረኩ የተገኙት የሀዲያ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ቦጋለ ባደረጉት ንግግር፤ የሀዲያ የዘመን አቆጣጠር ወቅቶችን መሰረት ያደረገ መሆኑን ጠቁመው፣ በዓሉ መስከረም በገባ በሁለተኛው ሳምንት ጀምሮ እንደሚከበር ገልጸዋል።
​“ያሆዴ” ከአሮጌው ወደ አዲስ ዘመን መሸጋገሪያ ብቻ ሳይሆን የማህበረሰቡን አብሮነት፣ ፍቅርና መተሳሰብ እንዲሁም የወንድማማችነትና የእህትማማችነት እሴቶችን የሚያጠናክር ታላቅ ባህላዊ ሀብት መሆኑንም አብራርተዋል።
​የሀዲያ ዞን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ እቴነሽ ሙሉጌታ በበኩላቸው፤ “ያሆዴ” በማህበረሰቡ ዘንድ በታላቅ ጉጉት የሚጠበቅ፣ አሮጌውን ዘመን በይቅርታና በእርቅ ሽኝቶ ወደ አዲሱ ዘመን የሚሸጋገሩበት ድልድይ መሆኑን ገልጸዋል።
​በዓሉ በሁሉም የዕድሜ ክልል በሚገኙ የብሔሩ ተወላጆች ዘንድ የሚከበርና የሕዝቦችን የእርስ በርስ መስተጋብር፣ መከባበርንና ሰላምን የሚያጎለብት ትሩፋት እንዳለው ተናግረዋል።
​በተጨማሪም የሀዲያ፣ የሲዳማና የኦሮሚያ ብሔሮች የባህል ሽማግሌዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንዲሁም ከሻሸመኔ፣ ከወንዶገነት፣ ከኩየራ፣ ከአርሲ ነገሌና ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ የብሔሩ ተወላጆችና የአካባቢው ነዋሪዎች የበዓሉ ታዳሚ ሆነዋል። (የሀዋሳ ከተማ ኮሙኒኬሽን)


አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ