ግፋታ የአንድነትና የፍቅር በዓል በመሆኑ ለሀገራችን አንድነት መሠረት ነው -ጥላሁን ከበደ

ግፋታ የአንድነትና የፍቅር በዓል በመሆኑ ለሀገራችን አንድነት መሠረት ነው -ጥላሁን ከበደ
ግፋታ የአንድነትና የፍቅር በዓል በመሆኑ ለሀገራችን አንድነት መሠረት ነው -ጥላሁን ከበደ
*******
ሀዋሳ፣ መስከረም 10፣2019 (ኤስቢሲ) ግፋታ የአንድነትና የፍቅር በዓል በመሆኑ ለሀገራችን አንድነት መሠረት ነው ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ጥላሁን ከበደ ተናግረዋል።
የወላይታ ብሔር ዘመን መለወጫ "ግፋታ" በወላይታ ሶዶ ስታዲዬም ተከብሯል።
ግፋታ የይቅርታና የእርቅ በዓል በመሆኑ ለሀገራዊ አንድነት የጎላ ሚና አለው ያሉት አቶ ጥላሁን ክልሉ በዓላትን ከባህላዊ እና ከታርክ ቅርስነት ባሻገር ለሀገራዊ ሰላምና ልማት ለመጠቀም ይሰራልም ብለዋል
በክልሉ ያሉ በርካታ ብሔር ብሔረሰቦች ያሏቸውን ባህላዊ እሴቶችን በመጠቀም ለአንድነትና ለጋራ ብልጽግና ማዋል ያስፈልጋልም ሲሉ ተናግርዋል።
በመርሃግብሩ የሲዳማ ብሔር ተወካዮችም በክልሉ ምክትል ፕሬዚደንትና ትምህርት ቢሮ ኃላፊ በአቶ በየነ ባራሳ የተመሩ ስሆኖ ሁለት ሰንጋዎችን ሰጦታ አበርክተዋል።
በይስሐቅ ፍቅሩ


አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ