በዲጂታል ኢትዮጵያ ዕቅድ ማዕቀፍ ውስጥ የሳይበር ደህንነት ላይ ያተኮረ ስልጠና ለሲዳማ ክልል ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች እየተሰጠ ይገኛል

በዲጂታል ኢትዮጵያ ዕቅድ ማዕቀፍ ውስጥ የሳይበር ደህንነት ላይ ያተኮረ ስልጠና ለሲዳማ ክልል ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች እየተሰጠ ይገኛል

በዲጂታል ኢትዮጵያ ዕቅድ ማዕቀፍ ውስጥ የሳይበር ደህንነት አቅም ግንባታ ስልጠና ለሲዳማ ክልል ከፍተኛ አመራሮችና ጉዳዩ ለሚመለከታቸው ባለሙያዎች እየተሰጠ ይገኛል።
የሲዳማ ክልል ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀገረጽዮን አበበ በስልጠናው መድረክ መክፈቻ ንግግራቸው እንደገለጹት ስልጠናው የተዘጋጀው በአገራችን የዲጂታል ለውጥን ለማፋጠን በተጀመረው የ“ዲጂታል ኢትዮጵያ” እቅድ አቅጣጫ መሠረት ሲሆን የሳይበር ደህንነት ግንዛቤና አቅም ማጠናከር የዘመኑ አስፈላጊ ጉዳይ ስለሆነ ነዉ ብለዋል።
አክለውም ዛሬ ቴክኖሎጂ በፍጥነት እየሰፋ ሲሄድ መረጃን በደህንነት መጠቀም ከቴክኖሎጂው የበለጠ ትኩረት የሚፈልግ ጉዳይ በመሆኑ አመራር አካላትና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁሉ በመረጃ አስተዳደርና አጠቃቀም ላይ ልዩ ጥንቃቄ ለማድረግ በሳይበር ደህንነት ዙሪያ አስፈላጊውን ግንዛቤ መጨበጥ እጅግ አስፈላጊ እንደሆነም አስረድተዋል።
የተሳሳተ መረጃ ስርጭት፣ የመረጃ ጥቃት እና የዲጂታል ስርዓቶች መዳከም በተቋማት ላይ ብቻ ሳይሆን በሰፊው ማህበረሰብ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ሊያመጣ እንደሚችል የገለጹት ኃላፊዋ እንደ ክልል በዲጂታል ቴክኖሎጂ የሰው ኃይል አቅም መገንባትና ማጠናከር ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሆነ በመግለጽ ስልጠናው በተቋማት ውስጥ የመረጃ ጥበቃ ባህልን ለማሳደግ እና የዘመኑን የሳይበር ፈተናዎችን በእውቀት ለመመከት የሚያግዝ ነው ብለዋል።
ስልጠናው በሲዳማ ክልል ሳይንስና ኢኖቬሽን ኤጄንሲ እና በInformation Network Security Administration /INSA/ ባለሙያዎች የተመራ ሲሆን ዋና ዓላማው የዲጂታል መረጃ ጥበቃን ማጠናከር፣ የሳይበር ደህንነት ንቃተ-ህልና መገንባት እና የመረጃ አስተዳደር ደህንነትን በተመለከተ ግንዛቤ ማሳደግ እንደሆነ ተገልጿል።
በስልጠናው ወቅት የሳይበር ጥቃት አይነቶችና መከላከያ መንገዶች፣የማህበራዊ ሚዲያ መረጃ ደህንነት፣የተሳሳቱ መረጃዎችን (disinformation) መለየት፣የመንግሥት መረጃ ስርዓቶች ጥበቃ የዲጂታል ሥነ-ምግባር የሚሉ ጉዳዮች በስፋት ተዳስሷል።
የዲጂታል መዋቅሮች እየተስፋፉ ባሉበት ዘመን የሳይበር ደህንነት ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠት አስፈላጊ በመሆኑ በየተቋሙ የመረጃ ጥበቃ ሥርዓቶችን ለማጠናከር ወሳኝ ጉዳይ እንደሆነም ተብራርቷል (ሲ/መ/ኮ/ቢ)።


አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ