በተፈጥሮ የጤና ችግር ያለባቸው ዜጎች የተሻለ ህክምና አግልግሎት አግኝተው ጤናማ ህይወት እንዲኖሩ ለማድረግ ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ይገኛል

በተፈጥሮ የጤና ችግር ያለባቸው ዜጎች የተሻለ ህክምና አግልግሎት አግኝተው ጤናማ ህይወት እንዲኖሩ ለማድረግ ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ይገኛል

የአፈጣጠር ችግር ያለባቸው ዜጎች በቴክኖሎጂ የታገዘ የተሻለ ህክምና አግልግሎት እንዲያገኙ ለማስቻል ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ገለፀ።
ቢሮው ከሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በተፈጥሮ የከንፈርና ላንቃ መሰንጠቅ እንዲሁም ተያያዥ ችግሮች ያሉባቸው ዘጎች የተሻለ ህክምና አግኝተው ጤናማ ህይወት እንዲኖሩ ለማስቻል የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም አድርጓል ።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ልዩ አማካሪ የሆኑት ፕ/ር ስለሺ ጋሮማ፣ ከዚህ ቀደም በአገራችን ላይ የነበረዉ የጤና ተደራሽነት እና የአግልግሎት አሰጣጥ ፖሊሲ እንዲሻሻል በጤና ሚኒስቴር ደረጃ ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ መቆየታቸውን አንስተው በሁሉም ክልሎች ላይ የሚገኙ የጤና አግልግሎት ሰጪ ተቋማት በተፈጥሮ የአፈጣጠር ችግር ያለባቸው ዜጎች ላይ ልዩ ትኩረት በማድረግ የተሻለ የህክምና አግልግሎት እንዲያገኙ ለማስቻል በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል ።
የጤና ሚኒስቴር የህክምና አግልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢሊባቡር ቡኖ ( ዶ/ር) በበኩላቸው የከንፈርና ላንቃ መሰንጠቅ ችግር የሚያጋጥማቸው ህፃናት ልዩ ህክምናና ድጋፍ እንዲያገኙ ለማድረግ በሚኒስቴሩ ደረጃ ግብረሃይል ተቋቁሞ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል ።
የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሙንጣሻ ብርሃኑ በህፃናት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ እና ህፃናት ጤናማ ሆነው
እንዲያድጉ ለማድረግ ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት የተለያዩ ስራዎች እየተሠራ መቆየቱን ገልፀው በአሁኑ ግዜ ከአላቲዮን አጠቃላይ ሆስፒታል ጋር በመተባበር ነፃ የህክምና አግልግሎት እየተሰጠ እንደሚገኝም አስረድተዋል።
በአሁኑ ሰአት በአላቲዮን አጠቃላይ ሆስፒታል ነፃ የህክምና አግልግሎቱን እያገኙ ያሉ ታካሚዎች በበኩላቸው ከዚህ በፊት የአፈጣጠር ችግር ያለባቸው ዜጎች ከማህበረሰቡ እንዲገለሉ የማድረግ አይነት እንቅስቃሴዎች በማህበረሰቡ ዉስጥ መኖሩን ጠቅሰዋል።
መንግስት ያመቻቸውን ነፃ የጤና አግልግሎት በማግኘታቸው ደስተኞች ከመሆናቸው ባለፈ ሌሎችም ዜጎች የተሰጠውን ዕድል በመጠቀም እንዳለባቸውም ታካሚዎቹ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።


አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ