ከጥበብ ቀላያት ጠል የፈሰሰለት የዘመን አቆጣጠር

ከጥበብ ቀላያት ጠል የፈሰሰለት የዘመን አቆጣጠር

የሲዳማ ህዝብ ለበርካታ ዘመናት ከአያት ከ አባቶቹ በወረሰው ጥበብ የጨረቃና የከዋክብትን ኡደት ተከትሎ ዘመን ይቀምራል።
‎ፊቼ ጨምበላላ ለሲዳማ ህዝብ የአዲስ ዘመን ብስራት፣ የዘመን አሀዱ ጮራ ፣ከአሮጌው አመት ወደ አዲስ ዘመን መሸጋገሪያ ድልድዩ ነው።
‎አለም በብዙ መሳሪያና ዘመናዊ ዕውቀት ጠፈርን ሲመራመር የሲዳማ ጠበብት አባቶች (አያንቶዎች) የከዋክብትን ና የጨረቃን አቀማመጥ በመመልከት ደቂቃ ና ሰዓታትን በመቀመር ፣የምድርን ፣የፀሐይንና የጨረቃን ኡደት የወቅቶችን አመጣጥ ስርዓት የማወቅ ጥበብን የታደለ ህዝብ ነው።
‎ፊቼ ጨምበላላ እጅግ ረቂቅ የሆነውን የሲዳማ አባቶችን የስነ ፈለግ ዕውቀት ነፀብራቅን ለ አለም ያበራ በዓል ከመሆኑም ባሻገር የዕውቀት ፍልስፍናን ለሌሎች ያሳየ፣በከዋክብት በጨረቃ ኡደት ዘመን በመቀመር አለምን አጀብ በማሰኘት በተባበሩት መንግስታት በአለም የትምህርት ፣የሳይንስ እና ባህል ድርጅት UNESCO የተመዘገበ ከሲዳማ ቅርስነት አልፎ አለም የደመቀበት ድንቅ ጥበብ ሆኗል።
‎በናርዶስ አየለ


አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ