የገጠር ሞዴል ቤቶችን ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞና የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ(ዶ/ር) ለተጠቃሚዎች አስረከቡ

የገጠር ሞዴል ቤቶችን ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞና የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ(ዶ/ር) ለተጠቃሚዎች አስረከቡ

በደቡባዊ ሲዳማ ዞን ዳራ ወረዳ በማጪሾ ቀበሌ በገጠር ኮሪደር ልማት እሳቤ የተገነቡ የገጠር ሞዴል ቤቶችን ነዉ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞና የኢፌዴሪ ፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ(ዶ/ር) ለነዋሪዎች ያስረከቡት ።
ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በመርሃ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ በብልፅግና ፓርቲ የሚመራው መንግሥት የአርሶና አርብቶ አደሩን የኑሮን ዘይቤ ለመቀየር የገጠር ሞዴል ቤቶችን ግንባታ ማስጀመሩን ተናግረዋል ።
የገጠር ሞዴል ቤቶች ለማኅበረሰቡ ዘመናዊ፣ ጤናማ፣ ጽዱ እና ምቹ የመኖሪያ ከባቢ ለመፍጠር እድል የሚሰጥ ነው ሲሉ ርዕሰ መስተዳድሩ ገልፀዋል።
የኢፌዴሪ ፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ(ዶ/ር) በበኩላቸው የገጠር ሞዴል ቤቶቹ የአርሶና አርብቶ አደሩን የኑሮ ዘይቤ የሚያሻሽል እንደሆነ ገልፀዋል።
ቤቶቹ በፕላንና ልማት ሚኒስቴርና በተጠሪ ተቋማት ድጋፍ የተገነቡ ሲሆን መንግሥት የአርሶ አደሩንና የአርብቶ አደሩን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ በልዩ ንድፍ የተገነቡ ሞዴል ቤቶች ናቸው ሲሉ አክለዋል ።


አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ