በዜጎች የሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ያላቸው ሚና የጎላ ነው" ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ።

በዜጎች የሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ያላቸው ሚና የጎላ ነው" ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ።

በዜጎች የሥራ እድል ፈጠራ ላይ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ያላቸው ሚና የጎላ መሆኑን የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ገለጹ።
በሲዳማ ክልል የዜጎችን ተጠቃሚነትና ተሳተፎ ለማረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱት መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማት በክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ የምስጋናና ማበረታቻ ፕሮግራም ተካሂዷል።
በምስጋናና እውቅና ፕሮግራም ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ እንደገለጹት ለዜጎች የሥራ እድል ለመፍጠር መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ለተጫወቱት ሚና አመስግነው በክልላችንም ሆነ በሀገራችን የሥራ እድል ለመፍጠርና የዘጎችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል መንግስት ከፍተኛ ሥራ እየሠራ መቆየቱን ጠቅሰዉ ሥራዎች እየተሠሩ ቁልፍ ማነቆ የሆነውን የፋይናንስና የቴክኒክ ችግሮችን በመለየት መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ደግሞ በመንግስት ጎን በመሆን የላቀ ውጤት እንዲመዘገቡ አድርገዋል ብለዋል።
ከዚህ ቀደም በሥራ እድል ፈጠራ ላይ ባደረግነው ግምገማ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የተወጡት ሚና የጎላ መሆኑን ለይተናል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ አሁንም ድጋፋቸው ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።
የሲዳማ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀገረጽዮን አበበ በበኩላቸው የሥራ እድል ለመፍጠር በሀገር ደረጃ የተሠጠውን ትኩረት እና በክልሉ ያለውን የሥራ ፍላጎት ከግምት ውስጥ በማስገባት በርካታ ችግሮችን የመፍታት ሥራ መሠራቱን ተናግረው ለዚህ መንግስታዊ ያልሆኑና የግል ድርጅቶች የተወጡት ሚና የጎላ መሆኑን ገልጸዋል።


አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ