ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ ከእስራኤል አቻቸው ጋር ተወያዩ

ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ ከእስራኤል አቻቸው ጋር ተወያዩ

ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ በኢትዮጵያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙትን የእስራኤል ፕሬዚዳንት አይዛክ ሄርዞግን በመቀበል በሁለቱ ሀገራት ታሪካዊና ባህላዊ ትስስር ዙሪያ ሰፊ ውይይት አካሂደዋል።
በውይይቱ ወቅት በተለይም የእስራኤል ተወላጅ የሆኑ የቤተ-እስራኤል ማኅበረሰብ አባላት በሁለቱ ሀገራት መካከል እንደ አንድ "ሕያው ድልድይ" በመሆን ያላቸውን ሚና ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ትኩረት እንደተሰጠው ፕሬዚዳንት ታየ በማኅበራዊ ትስስር ገጽ ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸዋል።
ይህ ጉብኝት ለዘመናት የዘለቀውን የሁለቱን ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደ አዲስ ምዕራፍ እንደሚያሸጋግረው ይጠበቃል።


አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ