ኢትዮጵያና አሜሪካ የ1 ነጥብ 466 ቢሊየን ዶላር የትብብር ስምምነት ፈረሙ::

ኢትዮጵያና አሜሪካ የ1 ነጥብ 466 ቢሊየን ዶላር የትብብር ስምምነት ፈረሙ::

ኢትዮጵያ እና አሜሪካ የ1 ነጥብ 466 ቢሊየን ዶላር ትብብር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።
የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያ ለጤናው ዘርፍ ልማት ትብብር የሚውል የ 1 ነጥብ 01 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ይፋ አድርጓል።
ትብብሩ ለአምስት ዓመት ለጤና ዘርፍ ዘላቂ ልማት እና የጋራ ኢንቨስትመንት ማጠናከሪያ ትብብር የሚውል ነው።
የመግባቢያ ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ፣ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ እና በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ ፈርመዋል።
ድጋፉ በኢትዮጵያና አሜሪካ ትብብር ታሪካዊ የተባለለት ሲሆን የአዲሱ የትብብር ምዕራፍ የጠበቀ ግንኙነት ማሳያ እንደሆነም ተነስቷል።
120 ዓመታትን የተሻገረው የኢትዮጵያ እና አሜሪካ ወዳጅነት በተለያዩ የትብብር መስኮች ሲገለጥ መቆየቱ ይታወሳል።


አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ