በሀዋሳ ከተማ የኑሮ ውድነትን ለማቃለልና እና ተገቢ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪን ተቆጣጥሮ ለማስቀረት ከፍተኛ ሥራ መሰራት እንዳለበት የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ ተናገሩ።

በሀዋሳ ከተማ የኑሮ ውድነትን ለማቃለልና እና ተገቢ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪን ተቆጣጥሮ ለማስቀረት ከፍተኛ ሥራ መሰራት እንዳለበት የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ ተናገሩ።

በሀዋሳ ከተማ የኑሮ ውድነትን ለማቃለልና እና ተገቢ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪን ተቆጣጥሮ ለማስቀረት ከፍተኛ ሥራ መሰራት እንዳለበት የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ ተናገሩ።


********

ሀዋሳ፣ ነሐሴ 15/2018 ዓ/ም (ኤስቢሲ) 


የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ንግድ እና ገበያ ልማት መምሪያ፣ ከባለድርሻ አካላት ጋር በ2018 ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 ዕቅድና ግብን በማስቀመጥ ላይ ያተኮረ ዓመታዊ የንግድ ጉባኤ አካሂዷል።


በመድረኩ፣ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ፣ በከተማዋ የሚሰሩ የተለያዩ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች የዜጎችን ህይወት እንዲቀይሩ የታለሙ እንደሚሆኑ ተናግረዋል።


አቶ ጥራቱ ከቅርብ ግዜ ወዲህ በከተማዋ የንግድ ሱቆች እና የህንፃዎች ኪራይ ላይ ከፍተኛ ጭማሪ የሚስተዋል ችግር እንደሆነ ተናግረው፣ የጭማሪውን መጠን እና ፍጥነቱን ለመግራት ጠንከር ያለ እርምጃ ይወሰዳል ሲሉ አሳስበዋል።


ሀዋሳ ፈጣን እድገት ላይ እንደምትገኝና እድገቱም ለውጡም ሙሉ እንዲሆን፣ የንግዱ ዘርፍ ስርዓት እና አጠቃላይ ኢኮኖሚው ፍትሃዊ እና ግዜውን የሚመጥን ዘመናዊ መሆን እንዳለበት የሀዋሳ ከተማ ም/ ከንቲባ እንዲሁም የንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ሀላፊ አቶ አገና ነቶ ተናግረዋል።


አቶ አገና አክለውም፣ ህገወጥ ነጋዴዎች በህጋዊዎቹ ነጋዴዎች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደሩ ስለሆነ ፍትሀዊነትን ለማረጋገጥ ሁሉም ነጋዴ ህጋዊ መሆን አለበት ብለዋል።


ገቢ ለማመንጨትና ለማሳደግም ቁልፍ ሚና ስለሚጫወት፣ የግብይት ስርዓቱን በቴክኖሎጂ የተደገፈ እና ዘመናዊ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን አብራርተዋል።


የመድረኩ ተሳታፊ ባለድርሻ አካላት በየበኩላቸው በሰጡት አስተያየት፣ በሐዋሳ ከተማ የሚታየውን የኑሮ ውድነት በማሻሻል እንዲሁም ገበያውን በማረጋጋት ላይ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለበት እና ለስኬቱም ከሁሉም ባለድርሻ አካል ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።


በመድረኩ፣ የኑሮ ውድነትን በማረጋጋት ረገድ የላቀ አፈፃፀም ለነበራቸው ነጋዴዎች እና ማህበራት እውቅና የመስጠት ስነ ስርዓትም ተካሂዷል።


ማርያማዊት ብፅዓተ


ለሃሳብ ልዕልና 


ቀጣዮቹን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን የኤስቢሲ ቤተሰብ ይሁኑ! 


Facebook: -

https://www.facebook.com/profile.php?id=61563363361689 https://www.facebook.com/profile.php?id=100064075051944

YouTube: -

https://youtu.be/fUjnn1dQLg8?si=1bzb_8Nx8mnC-Vk5

Telegram: - https://t.me/sbcnewmedia

WhatsApp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaZ2D6NH5JLsF9xJaB



አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ