የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የወባ በሽታን ለማስወገድ የብዙ ዘርፍ ትብብርን በመደገፍ የምክክር አውደ ጥናት መድረክ አካሄደ።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የወባ በሽታን ለማስወገድ የብዙ ዘርፍ ትብብርን በመደገፍ የምክክር አውደ ጥናት መድረክ አካሄደ።
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የወባ በሽታን ለማስወገድ የብዙ ዘርፍ ትብብርን በመደገፍ የምክክር አውደ ጥናት መድረክ አካሄደ።
*********
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የወባ በሽታ እና ሌሎች በቬክተር የሚተላለፉ በሽታዎች ምርምር ማዕከል (MVBDRC) ከምርምር እና ትብብር ምክትል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት (VPRC) ጋር በመተባበር፣ የወባ በሽታን ለማስወገድ የብዙ ዘርፍ ትብብርን በመደገፍ ላይ ከሲዳማ ክልል የተውጣጡ ቁልፍ የጤና ዘርፍ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የምክክር አውደ ጥናት አካሂዷል ።
በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የምርምር እና ትብብር ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታፈሰ ማቴዎስ በመክፈቻ ንግግራቸው፣ የማህበረሰብ ጤና ችግሮችን መፍታት ለሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋና ተቋማዊ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ በመሆኑን አፅንዖት ሰጥተዋል ያሉት ምክትል ፕረዝዳንቱ የወባ በሽታ እና ሌሎች በቬክተር የሚተላለፉ በሽታዎችን ለማስቀረት እና በሽታውን ለመዋጋት እንድሁም ሀገራዊ ዘላቂ ግቦቻችንን ለማጠናከር ከሁሉም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር እየሰሩ መሆኑን ተናግርዋል ።
በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የማዕከሉ ዳይሬክተር እና ተመራማሪ ዶ/ር ዳዊት ሃዋሪያ የአካባቢ እና ብሔራዊ የወባ አዝማሚያዎችን፣ ተዛማጅ የሰው ልጅ ተግዳሮቶች ሊሆኑ የሚችሉትን የሚወገዱበት መንገዶችን የሚተነትኑ ተጨባጭ ማስረጃዎችን አቅርበዉ ፣ በ2030 ወባን ለማስወገድ ዓለም አቀፍ ግቦች ቢኖሩም፣ ዓመታዊ መጠን እየጨመረ በዒላማዎች እና በመሬት እውነታ መካከል ያለውን ክፍተት እንደሚያመለክት አፅንዖት ሰጥቶ መሰራት እንዳለበት ጠቁመዋል።
መድረኩ ላይ የተገኙት በሲዳማ ክልል የጤና ቢሮ የበሽታ መከላከል እና ቁጥጥር ዳይሬክተር፣ ቃርሳ ዳፉሳ እንዳሉት እንደ ክልልም የወባ በሽታ ለማጥፋት ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸዉን ገልፀዉ፣ በእለቱ በዉይይቱ ላይ የተነሱትን ሀሳቦች ወደ ታች በማዉረድ ተግባራዊ መደረግ እንዳለበትም አሳስበዋል ።
ተሳታፊዎች የወባ በሽታን የማስወገድ ግብን ለማሳካት የሚመለከታቸው የመንግስት እና የማህበረሰብ ዘርፎች ውስጥ ስትራቴጂካዊ፣ ባለብዙ ዘርፍ ትብብር እና የጤና ተሟጋችነትን ማካተት አስፈላጊ በመሆኑን ሀላፊነታቸዉን እንደሚወጡ ተናግረዋል።
ዳንኤል ሂርጳቶ
ለሃሳብ ልዕልና
ቀጣዮቹን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን የኤስቢሲ ቤተሰብ ይሁኑ!

አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ