የለኩ ከተማ አስተዳደር የ10 ዓመት የፕላን እቅድ ይፋ አደረገ።

የለኩ ከተማ አስተዳደር የ10 ዓመት የፕላን እቅድ ይፋ አደረገ።

የለኩ ከተማ አስተዳደር የ10 ዓመት የፕላን እቅድ ይፋ አደረገ።

**********   

ሀዋሳ፣ ነሐሴ 11፣ 2018 (ኤስቢሲ) በሲዳማ ክልል ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን የለኩ ከተማ አስተዳደር ከተማዋን ዘመናዊና ተወዳዳሪ ለማድረግ ያለመ የ10 ዓመት የፕላን እቅድ ለህዝብ ይፋ አደረጓል።


በእቅዱ የከተማዋን መሰረተ ልማት ማሻሻል፣ ዘመናዊ የከተማ አስተዳደርን ማጠናከርና ከተማዋን ተወዳዳሪ የልማት ማዕከል ማድረግ ትኩረት የተሰጣቸው ጉዳዮች ናቸው።


በመድረኩ የተገኙት የሲዳማ ክልል ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ብሩክ ሰለሞን፣ የከተሞችን ዕድገት እውን ለማድረግ የክልሉ መንግስት ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። 


የለኩ ከተማ የ10 ዓመት የፕላን እቅድም በተግባር እንዲውል በማድረግ ከተማዋን በመሰረተ ልማትና በዘመናዊ አገልግሎቶች የተሻለች ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።


የክልሉ የከተማና ፕላን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተገኔ ታደሰ በበኩላቸው፣ የከተሞች ፕላን ለረጅም ጊዜ ሲዘጋጅ የቆየ ቢሆንም ይህ እቅድ ለለኩ ከተማ ዕድገት አስፈላጊ መፍትሄ የሚሰጥ መሆኑን ጠቁመዋል።


የለኩ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ነፃነት ሾንኮራ በበኩላቸው፣ ከተማዋን በፕላን የሚመራትና ተወዳዳሪ ከተማ ለማድረግ እንደሚሰሩ ገልጸዋል።


በመድረኩ የተሳተፉ ነዋሪዎችና አካላት በበኩላቸው፣ የቀረበው የ10 ዓመት የፕላን እቅድ ከከተማዋ ነባራዊ ሁኔታና የወደፊት ዕድገት ጋር የሚጣጣም በመሆኑ መደሰታቸውን ገልጸዋል።


መቻል ሌዳሞ


ለሃሳብ ልዕልና 


ቀጣዮቹን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን የኤስቢሲ ቤተሰብ ይሁኑ! 


Facebook: -

https://www.facebook.com/profile.php?id=61563363361689 https://www.facebook.com/profile.php?id=100064075051944

YouTube: -

https://youtu.be/fUjnn1dQLg8?si=1bzb_8Nx8mnC-Vk5

Telegram: - https://t.me/sbcnewmedia

WhatsApp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaZ2D6NH5JLsF9xJaB1



አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ