ምክክሩ ልዩነትን በሀሳብና በውይይት ለመፍታት የሚያስችል ትልቅ ሚና ያለው ነው ፡- የምክክሩ ተሳታፊዎች

ምክክሩ ልዩነትን በሀሳብና በውይይት ለመፍታት የሚያስችል ትልቅ  ሚና ያለው ነው  ፡- የምክክሩ ተሳታፊዎች
‎የሀገራዊ ምክክር ሂደቱ በተቀመጠለት መርሃ-ግብር መሠረት እየተካሄደ ይገኛል ።
‎ምክክሩ ልዩነቶችን በሀሳብና በውይይት ለመፍታት የሚያሰችል ትልቅ ሚና ያለው ነው ያሉት የምክክሩ ተሳታፊዎች የአንዱ ሀሳብ ጎልቶ የበላይነት የሚንፀባረቅበት ሳይሆን የሌላውን ሀሳብ የጋራ አድርጎ በመመካከር መተማመን ላይ እየተደረሰበት ያለ የነገ ኢትዮጵያን በጋራ በአንድነት ፅኑ መሠረት ላይ ለመገንባት የሚያስችል እንደሆነ ተናግረዋል።
‎ምክክሩ በየደረጃው አጀንዳዎቹ ላይ የተለያዩ የሀሳብ መንሸራሸር እየታየበት ያለና አከራካሪ ጉዳዮች ላይ በጥልቀት በመመካከር የትኛውንም አካል በማይጎዳ መንገድ የጋራ መግባባት ላይ እየተደረሰ እየቀጠለ ነው ብለዋል።
‎በቀጣይ የምክክሩ ሂደት ውጤታማና የተሳካ እንደሆን ሁሉም ሀገራዊ አንድነትን በማስቀደም በሠከነ መንገድ መመካከሩን መቀጠል እንዳለበትም ተመካካሪዎቹ አስተያየት ሰጥተዋል ።


አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ