ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በባሕር ዳር ከተማ ቁልፍ የልማት ቦታዎችን ጎበኙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በባሕር ዳር ከተማ ቁልፍ የልማት ቦታዎችን ጎበኙ

የጥቁር ውሃ- ሐዋሳ ኃይሌ ሪዞርት መገንጠያ መንገድ መልሶ-ግንባታ ፕሮጀክት በትኩረት እየተከናወነ ነው-በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር 

********

 

ሀዋሳ፣ ነሐሴ 12፣ 2018 (ኤስቢሲ)፦ በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት በራስ-ኃይል እየተገነባ የሚገኘው የጥቁር ውሃ – ሐዋሳ ኃይሌ ሪዞርት መገንጠያ የመንገድ መልሶ-ግንባታ ፕሮጀክት አፈጻጸም 40 በመቶ መድረሱ ገልጿል።

 

ይህ 1.1 ኪሎ ሜትር ርዝመት እና 26 ሜትር ስፋት ያለው የመንገድ ፕሮጀክት፤ በሐዋሳ ከተማ መግቢያና መውጫ እንዲሁም በሐዋሳ ሐይቅ ዳርቻ አካባቢ ቀደም ሲል በክረምት ወቅት ይታዩ የነበሩትን የጎርፍ መጥለቅለቅ፣ የውኃ ክምችት እና የመንገድ መበላሸት ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ያለመ ነው። 


በአካባቢው ከሐይቁ አቅጣጫ የሚመጣው ውሃ ነባሩን የመንገድ መዋቅር አልፎ መሄድ ባለመቻሉ፣ መንገዱ በውሃና በደለል ተውጦ ለነዋሪዎችና ለተሽከርካሪዎች ከፍተኛ ችግር መፍጠሩ ይታወሳል። ይህም በከተማዋ የቱሪስት መስህብ ገጽታና ውበት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ አሳድሮ ቆይቷል።

 

ይህንን የጎርፍ መጥለቅለቅ ችግር ለመቅረፍ የመንገዱ ከፍታ ከቀድሞው በ2 ሜትር ከ40 ሴንቲሜትር ከፍ እንዲል ተደርጎ እየተገነባ ይገኛል። በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ የሙሌት፣ የኮሪደር እና የውኃ ማፍሰሻ ሥራዎች በትኩረት እየተከናወኑ ናቸው።

 

በሰኔ ወር 2018 ዓ.ም አጋማሽ ላይ በሙሉ አቅም የተጀመረው ይህ ግንባታ በአጭር ጊዜ ውስጥ 40 በመቶ አፈጻጸም ላይ ደርሷል። የነዳጅ እና የግብዓት እጥረት ተጽዕኖዎች ቢኖሩም፥ ዋና ዋና ሥራዎችን እስከ መስከረም ወር 2019 ዓ.ም ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሠራ ይገኛል። 


ለዚህ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ በፌደራል መንግሥት 334 ሚሊዮን ብር በጀት የተመደበለት ሲሆን፥ እስከአሁን ለ200 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር ችሏል።



አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ