በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን ፈቶ ስር ነቀል ለዉጥ ለማምጣት በልዩ ትኩረት እየተሠራ ነው፦የሲዳማ ክልል ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ።

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን ፈቶ ስር ነቀል ለዉጥ ለማምጣት በልዩ ትኩረት እየተሠራ ነው፦የሲዳማ ክልል ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ።
በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን ፈቶ ስር ነቀል ለዉጥ ለማምጣት በልዩ ትኩረት እየተሠራ ነው፦የሲዳማ ክልል ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ።
**********
ሀዋሳ፣ ነሐሴ 11፣ 2018 (ኤስቢሲ)
የሲዳማ ክልል ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የአመራሮችና ባለሙያዎች የ2018 ዓ.ም የስራ አፈፃፀምና የ2019 ዓ.ም እቅድ ላይ ከተቋሙ ሰራተኞች ጋር ዉይይት ተደርጓል።
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር መብራቴ መለሰ ተቋሙ ከተቋቋመበት ግዜ አንስቶ ከሰዉ ሀይል ሟሟላት ጀምሮ የግብአት አቅርቦት አንፃር አመርቂ ስራዎች መሠራታቸዉን ገልጸዉ ከምህንድስናና ተዛማጅ ጉዳዩች ፍቃድ አሠጣጥ ጋር ወጥ አካሄዶች ተዘርግተው ህገወጥ አካሄዶች እርምት ተደርጎባቸዋል በዚህም 50 የሚሆን ፍቃድ ተሰርዟል ብለዋል።
150 የሚሆኑ ፕሮጀክቶች ጥራታቸዉ ተጠብቆ እየተጠናቀቁ ይገኛሉ ለእነዚህም የቴክኒክ ክትትል ከማድረግ አንስቶ ህጋዊ መሠረታቸዉን ይዘዉ እንዲጠናቀቁ የተቋሙ ክትትል ትልቅ አበርክቶ አድርጓል።
የአገልግሎት አሠጣጥ ላይ ብዙ መሻሻሎች ቢኖሩም አልፎ አልፎ የሚስተዋሉ የሙስናና ብልሹ አሠራሮችን ከስር መሠረቱ ነቅሎ ለመጣል በቀጣይም ልዩ ትኩረት ይሻል ብለዋል።
ተቋሙ በባለፉት ግዜያት ከዋጋ ንረት ጋር ተያይዘዉ በዘርፉ ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን ክትትል በማድረግ ችግሮቹ የሚፈቱበትን ሁኔታዎች በማመቻቸት ብዙ ፕሮጀክቶች በስኬት እንዲጠናቀቁ ከማድረግ አንፃር የኮንስትራክሽን ባለስልጣኑ ሚና ከፍተኛ እንደነበር የገለፁት የግንባታ ፕሮጀክቶች ዲዛይንና ቁጥጥር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጉንሳሞ ጉሳ ሌሎች በርካታ ከደቡብ ክልል የተዛወሩ ዘርፈ ብዙ ችግሮች የነበሩባቸዉን ፕሮጀክቶችና በየወረዳዉ በተለያየ ምክንያት የተቋረጡ ፕሮጀክቶች በጥራት መጠናቀቃቸዉን ተናግረዋል።
ከኮርደር ዲዛይን እስከ የተለያዩ ፕሮጀክቶች እድሳት ድረስ ያሉ ትልልቅ ስራዎችንተቋሙ በአጭር ግዜ በስኬት እንዲያጠናቅቅ የመንግስት እገዛና ዉሳኔ ትልቅ አቅም መፍጠሩን ገልጸዋል።
ብሩክታዊት ብርሀኑ
ለሃሳብ ልዕልና
ቀጣዮቹን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን የኤስቢሲ ቤተሰብ ይሁኑ!

አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ