የሲዳማ ክልል ገንዘብ ቢሮ ለሜሪ ጆይ ኢትዮጵ በ5 ሚሊዮን ብር የጀነሬተር ድጋፍ አደረገ

የሲዳማ ክልል ገንዘብ ቢሮ ለሜሪ ጆይ ኢትዮጵ በ5 ሚሊዮን ብር የጀነሬተር ድጋፍ አደረገ


ሀዋሳ፣ ነሀሴ 07፣ 2018 (ኤስቢሲ) ‎የሲዳማ ክልል ገንዘብ ቢሮ ለሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ለኩላሊት እጠበት ማዕከል የሚሆን በ5 ሚሊዮን ብር የጀነሬተር ድጋፍ አድርጓል።

በመርሃ ግብሩ ‎የክልሉ ገንዘብ ቢሮ ሀላፊ አቶ ሀይሌ አርሲሳ በዚህ ወቅት እንደተናገሩት ህይወት ለማዳን ስራ ቅድሚያ በመስጠት ከፌዴራል ድጋፍ የተገኘውን 5 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የጀነሬተር ድጋፍ አድርገናል ብለዋል ።

‎ከዚህም ባለፈ የቢሮው አጠቃላይ ሰራተኞች በወር 200 ብር በማዋጣት ለማዕከሉ ድጋፍ አንደሚደረግ ገልፀዋል ።

‎አሁን ላይ የኩላሊት ህክምና ብዙ ወጪ የሚጠይቅና ፈታኝ በመሆኑ ይህንን ለማቅለል ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ የኩላሊት እጥበት ማዕከል ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሰራ ስለሚገኝ የክልሉ መንግስት ትኩረቱ ሰጥቷል ብለዋል።

‎የቢሮው ሀላፊው አክለውም ለማዕከሉ ግንባታ መጠናቀቅ አስፈላጊ ድጋፎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አንስተው ሁሉም ዜጋ ባለበት ሆኖ ለዚህ ማዕከል እጁን እንድዘረጋ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

‎ በኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ አገልግሎት የደቡብ ኢትዮጵያ ክላስተር አስተባባሪና የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት አምባሳደር የሆኑት አቶ ዘመን ለገሰ በበኩላቸው ሜሪ ጆይ በአሁኑ ሰዓት የኩላሊት አጥበት ስራዎችን እያስፋፋ እንደሚገኝና በቀጣይም ማዕከሉን ለማጠናከር ለሚደረገው ጥረት የተደረገው የጀነሬተር ድጋፍ ሚናው የጎላ መሆኑን አንስተዋል 

‎በኩላሊት ማዕከሉ ሀይል በሚቆራረጥበት ወቅት ለታካሚዎች የደም መርጋት እያስከተለ የደም ማቅጠኛ በመጠቀምና ተጨማሪ ፈሳሽ የማባከን ችግር እንደሚኖር ጠቅሰው በዛሬው ዕለት የተደረገው ድጋፍ ለህክምናው ሂደት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው ያሉት የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ኩላሊት እጥበት ማዕከል ሜድካል ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ኖቤል ናማራ ናቸው

‎ሠላማዊት ቲቦ


አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ