የሲዳማ ክልል መንገዶች ባለስልጣን ለአቅመ ደካማ ቤተሰብ የመኖሪያ ቤት ግንባታ አስጀመረ።

የሲዳማ ክልል መንገዶች ባለስልጣን ለአቅመ ደካማ ቤተሰብ የመኖሪያ ቤት ግንባታ አስጀመረ።
የሲዳማ ክልል መንገዶች ባለስልጣን ለአቅመ ደካማ ቤተሰብ የመኖሪያ ቤት ግንባታ አስጀመረ።
‎።።።።።።
‎ሀዋሳ፣ ነሐሴ 15/2018 ዓ/ም (ኤስቢሲ)
‎የሲዳማ ክልል መንገዶች ባለስልጣን በዳራ ኦትልቾ ወረዳ ለአንድ አቅመ ደካማ ቤተሰብ የመኖሪያ ቤት ግንባታ አስጀምሯል።
‎የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ማቲዎስ በየነ በመርሃ ግብሩ ላይ እንደገለጹት፣ ባለስልጣኑ ከዚህ በፊት ለአቅመ ደካማ ዜጎች ሁለት የመኖሪያ ቤቶችን ገንብቶ ማስረከቡን ገልጸዋል። በዳራ ኦትልቾ ወረዳ የተጀመረው የቤት ግንባታም የዚሁ የማህበራዊ ኃላፊነት ተግባር አካል መሆኑን ጠቁመዋል።
‎አቶ ማቲዎስ አክለውም ሁሉም የህብረተሰብ አካላት የመረዳዳትን ባህል በማጎልበት ለችግር የተጋለጡና አቅማቸው ደካማ የሆኑ ዜጎችን መደገፍ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።
‎በተመሳሳይ በዳራ ወረዳ በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የባለስልጣኑ አመራሮችና ሰራተኞች ችግኝ ተክለዋል።
‎ዋና ዳይሬክተሩ እንደገለጹት፣ ችግኝ የተተከለበት ቦታ ቀደም ሲል ባለስልጣኑ ለመንገድ ሥራ ጠጠር ሲያመርትበት የነበረና በዚህም የተነሳ የተጎዳ መሬት ነው። ቦታውን መልሶ ለማገገምና የአካባቢውን ስነ-ምህዳር ለመጠበቅ ችግኝ ለመትከል መምረጣቸውን ገልጸዋል።
‎የባለስልጣኑ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ አንድነት አሰፋ በበኩላቸው፣ የመኖሪያ ቤቱ ግንባታ የባለስልጣኑን ባለሙያዎችና ተሽከርካሪዎች በመጠቀም እየተከናወነ መሆኑን ገልጸው፣ ቤቱን በአጭር ጊዜና በጥራት ገንብተው ለተጠቃሚው ቤተሰብ እንደሚያስረክቡ ተናግረዋል።
‎በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሩም ሀገር በቀልና ድርቅን መቋቋም የሚችሉ የዛፍ ዝርያዎች መተከላቸውን ገልጸው፣ የተተከሉት ችግኞች እንዲጸድቁና እንዲያድጉ በቀጣይነት ክትትል እንደሚደረግባቸው አስታውቀዋል።
‎የሲዳማ ክልል መንገዶች ባለስልጣን በቤት ግንባታና በአረንጓዴ አሻራ ተግባራት በመሳተፍ፣ የማህበራዊ ኃላፊነትን ከመንገድ ልማት ሥራው ጎን ለጎን እያጠናከረ መሆኑን በመርሃ ግብሩ ተገልጿል።
ሲሳይ ከበደ
ለሃሳብ ልዕልና
ቀጣዮቹን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን የኤስቢሲ ቤተሰብ ይሁኑ!

አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ