የማህበረሰቡን የኑሮ ደረጃን ለማሻሻል በቀጣይነት በትኩረት እንደሚሰራ አቶ ፃድቁ ባጥሶ ተናገሩ።

የማህበረሰቡን የኑሮ ደረጃን ለማሻሻል በቀጣይነት በትኩረት እንደሚሰራ አቶ ፃድቁ ባጥሶ ተናገሩ።


ሀዋሳ:-ነሐሴ 5/2018 ዓ/ም (ኤስ ቢ ሲ)


የሰሜናዊ ሲዳማ ዞን በቀጣይ በስራ ላይ የሚውል የ መቶ ቀን እቅድ ላይ ውይይት አድርጓል ።


ያለንን ውስን መሬት በዘመናዊ መንገድ በማረስ ማህበረሰቡ በምግብ እራሳቸውን እንዲችሉ ለማድረግና ለስራ አጥ ወጣቶች የስራ እድል እንዲፈጠር የ መቶ ቀን እቅድ ተዘጋጅቶ በትኩረት እንደሚሰሩ የሰሜናዊ ሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ፃድቁ ባጥሶ ተናግረዋል ።


የህዝባችንን የመልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ ገቢን በአግባቡ ለመሰብሰብ በመቶ ቀን እቅድ መሠረት ቅድሚያ ሰጥተው እንደሚሰሩም አቶ ፃድቁ ጨምረው ተናግረዋል ።


ሕብረተሰብን ተጠቃሚ ለማድረግ ያለፈውን ዓመት እቅድ ተፈፃሚነትን በመገምገም በቀጣይ በቱሪዝምና በተለያዩ ስራ ዘርፎች በትኩረት እንደሚሰራም የሰሜናዊ ሲዳማ ዞን አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አበበ ይታደጉ ተናግረዋል ።


የህዝብን የመልማት ምቹ ሁኔታን ተጠቅመው ፈጣን ለውጥ ለማምጣት በመቶ ቀን እቅድ መሠረት ጠንክረው እንደሚሰሩም የመድረኩ ተሳታፊዎች ተናግረዋል ።


ኤርምያስ ሳንባቶ


ለሃሳብ ልዕልና 


ቀጣዮቹን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን የኤስቢሲ ቤተሰብ ይሁኑ! 


Facebook: -

https://www.facebook.com/profile.php?id=61563363361689 https://www.facebook.com/profile.php?id=100064075051944

YouTube: -

https://youtu.be/fUjnn1dQLg8?si=1bzb_8Nx8mnC-Vk5

Telegram: - https://t.me/sbcnewmedia

WhatsApp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaZ2D6NH5JLsF9xJaB1o



አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ