“ከተረጅነት ወደ ምርታማነት የተጀመረውን ጉዞ ከግቡ ለማድረስ በቁርጠኝነት እየተሰራ ነው” ሲሉ የሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ ገለጹ።

***************

ሀዋሳ- መስከረም 5 /1/2019 ዓ.ም(ኤሲቢስ)

በሲዳማ ክልል አደጋ ስጋት ኮሚሽን በተሰሩ የሥራ እንቅስቃሴዎችና በቀጣይ የሚከናወኑ ተግባራት ላይ የስትራቴጂ ኮሚቴው ግምገማ አካሂዷል።

በግምገማው ወቅት የኮሚቴው ሰብሳቢና የሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ፣ የዜጎችን የምግብ ዋስትና ማረጋገጥና ድንገተኛ አደጋዎች በሚከሰቱበት ጊዜ በራስ አቅም ለመመከት የሚያስችል አቅም መፍጠር ቀዳሚ ትኩረት መሆኑን ገልጸዋል።

በክልሉ በአደጋ ስጋት ቅነሳና በዜጎች የምግብ ዋስትና ዙሪያ የተጀመሩ ሥራዎችም ተጨባጭ ውጤት እያስገኙ መሆናቸውን አቶ አብርሃም ጠቁመዋል።

የሲዳማ ክልል አደጋ ስጋት ኮሚሽነር አቶ ሀይሉ ሀሰና በበኩላቸው፣ በኮሚሽኑ የተጀመሩ የአደጋ ስጋት ቅነሳና የዜጎችን ከተረጅነት ለማላቀቅ የሚያግዙ ሥራዎች በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥሉ የጋራ ርብርብ እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል።

 የክልሉ አቅምን በማጠናከር ዜጎችን ከተረጅነት ወደ ምርታማነት ማሸጋገርና የአደጋ ጊዜ መቋቋሚያ አቅምን ማሳደግ ቀጣይ የሥራ አቅጣጫ መሆኑ ተገልጿል።

ሙሉቀን ብርሃኑ

ቀጣዮቹን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን የኤስቢሲ ቤተሰብ ይሁኑ! 

Facebook: -

https://www.facebook.com/profile.php?id=61563363361689 https://www.facebook.com/profile.php?id=100064075051944

YouTube: -

https://youtu.be/fUjnn1dQLg8?si=1bzb_8Nx8mnC-Vk5

Telegram: - https://t.me/sbcnewmedia

WhatsApp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaZ2D6NH5JLsF9xJaB

አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ