የሚድሮክ ኢንዱስትሪ ግሩፕ ኤልፎራ መልጌ እርሻና አግሮ ፕሮሰሲንግ ፋብሪካ ለ600 በላይ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

የሚድሮክ ኢንዱስትሪ ግሩፕ ኤልፎራ መልጌ እርሻና አግሮ ፕሮሰሲንግ ፋብሪካ ለ600 በላይ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።
የሚድሮክ ኢንዱስትሪ ግሩፕ ኤልፎራ መልጌ እርሻና አግሮ ፕሮሰሲንግ ፋብሪካ ለ600 በላይ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።
ሀዋሳ- መስከረም 4 /1/2019 ዓ.ም(ኤሲቢስ)
በወንዶገነት ከተማ አስተዳደር የሚገኘው የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አካል የሆነው የኤልፎራ መልጌ እርሻ እና አግሮ ፕሮሰሲንግ ፋብሪካ፣ የ2019 የትምህርት ዘመን አስመልክቶ ከ600 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች የቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል ።
በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የፋብሪካው ኃላፊ ተወካይ አቶ ዮናስ ታደሰ እንደገለጹት፤ ተቋሙ ላለፉት አምስት ዓመታት ከሚያገኘው ገቢ ላይ በመቀነስ ለአቅመ ደካሞች ቤቶችን ሰርቶ ከማስረከብ ባለፈ ለተማሪዎች የሚሆን ዘላቂ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ እንዳደረገ ተናግረዋል ።
የኤልፎራ መልጌ እርሻ እና አግሮ ፕሮሰሲንግ ፋብሪካ ፣ የሕዝብ ግንኙነት እና ሕግ ዘርፍ አማካሪ የሆኑት አቶ ፍስሃ ፍሪሶ ፣ የሚድሮክ ኢንዱስትሪ ግሩፕ በዓመት ከሚያገኘው ገቢ 10 በመቶ ያህሉን ለማኅበራዊ ኃላፊነት ለበጎ አድራጎት ሥራዎች ላይ እንደሚያደርግ ገልፀዋል ።
የወንዶገነት ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ተወካይ አቶ ተመስገን ፀጋዬ በበኩላቸው፤ ፋብሪካው በተለያዩ ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ከሚያደርገው ተሳትፎ ባለፈ፣ በትምህርት ዘርፉ የሚሰሩ ሥራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ እያበረከተ ላለው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።
የድጋፉ ተጠቃሚ የሆኑት ተማሪዎች በበኩላቸው ለተደረገላቸው እገዛ ተቋሙን አመስግነው፤ የተበረከተላቸውን ቁሳቁስ በአግባቡ በመጠቀም ጠንክረው በመማር አገርና ማኅበረሰባቸውን ለመጥቀም እንደሚተጉ ገልጸዋል።
ገዛኸኝ ጋሻዉ
ቀጣዮቹን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን የኤስቢሲ ቤተሰብ ይሁኑ!

አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ