የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ የጳጉሜን 4 «የሕብረ ቀን» በተለያዩ በጎ ኩነቶች በዛሬው ዕለት አክብሯል።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ የጳጉሜን 4 «የሕብረ ቀን» በተለያዩ በጎ ኩነቶች በዛሬው ዕለት አክብሯል።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ የጳጉሜን 4 «የሕብረ ቀን» በተለያዩ በጎ ኩነቶች በዛሬው ዕለት አክብሯል።


**************

ሀዋሳ:- ጳጉሜ 04/13/2018 ዓ/ም(ኤስ ቢ ሲ)


በሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ አስተባባሪነት፣ በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ያሳተፈ የህብር ቀን አካል የሆነውን የበጎ አድራጎትና የሕዝባዊ አንድነት መርሃ-ግብር አካሂዷል ። 


የጳጉሜ 4 የሕብረ ቀንን መነሻ በማድረግ በተዘጋጀው በዚህ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት ሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሰላማዊት መንገሻ የክልሉ ጤና ቢሮ ከተለያዩ አጋርና አቻ ቢሮዎች ጋር በቅንጅት በመሥራት ዕለቱን በበጎ ተግባር ማድመቅ መቻሉን ገልጸዋል።


በተጨማሪም የጳጉሜ 4 ቀን በስፖርታዊ ሁነቶች ብቻ ሳይሆን በተጨባጭ የወገን ደራሽነት ስሜት መከበሩ የሕብረ ቀንን እውነተኛ ትርጉም የሚያሳይ መሆኑን አስረድተዋል።


የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ አገና ኔቶ በበኩላቸው የመረዳዳት፣ የመደጋገፍና የአብሮነት ዕሴቶች ከጥንት ጀምሮ የሲዳማም ሆነ አጠቃላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ መለያ የሆኑ ኩሩ ባህሎች መሆናቸውን ገልፀው አዲሱን ዓመት ስናከብር ፣ያገኘውም ይሁን ያጣው በአንድነትና በእኩልነት በዓሉን ማሳለፍ አለበት በማለት ተናግረዋል።


በበጎ አድራጎት ሥራዎቹ ላይ የተሳተፉት የከተማዋ ነዋሪዎችና ባለሙያዎች በበኩላቸው፣ 

ያላቸውን ለሌላቸው በማካፈል፣ በዓላትን በጋራና በአብሮነት ማሳለፍ የተለመደና ሊቀጥል የሚገባው የኢትዮጵያውያን የወል ስምምነት መሆኑን ገልፀው መጭውን የ2019 አድሱ ዓመት ሲያከብርም የተለያዩ በጎ ስራዎችን በመስራት ዜጎች ማሳለፍ እንዳለባቸው አሳስቧል ።


በገዛኸኝ ጋሻዉ


ቀጣዮቹን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን የኤስቢሲ ቤተሰብ ይሁኑ! 


Facebook: -

https://www.facebook.com/profile.php?id=61563363361689 https://www.facebook.com/profile.php?id=100064075051944

YouTube: -

https://youtu.be/fUjnn1dQLg8?si=1bzb_8Nx8mnC-Vk5

Telegram: - https://t.me/sbcnewmedia

WhatsApp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaZ2D6NH5JLsF9xJaB



አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ