የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሀዋሳ ዲስትሪክት «አዲሱን ዓመት በአገልጋይነት እና በበጎነት» በሚል መሪ ቃል ለአቅመ ደካሞች እና ለተቸገሩ ወገኖች የአዲስ ዓመት መቀበያ የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር አካሄደ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሀዋሳ ዲስትሪክት «አዲሱን ዓመት በአገልጋይነት እና በበጎነት» በሚል መሪ ቃል ለአቅመ ደካሞች እና ለተቸገሩ ወገኖች የአዲስ ዓመት መቀበያ የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር አካሄደ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሀዋሳ ዲስትሪክት «አዲሱን ዓመት በአገልጋይነት እና በበጎነት» በሚል መሪ ቃል ለአቅመ ደካሞች እና ለተቸገሩ ወገኖች የአዲስ ዓመት መቀበያ የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር አካሄደ።


**************

ሀዋሳ:- ጳጉሜ 03/13/2018 ዓ/ም(ኤስ ቢ ሲ)


ይህ የተከናወነው የበጎ አድራጎት መርሃ ግብር ተቋሙ ከትርፍ ባሻገር ለማኅበረሰቡ ያለውን የማይናወጥ ቁርጠኝነት እና ጥልቅ ማኅበራዊ ኃላፊነት በተግባር ያሳየበት ሆኗል።


የሲዳማ ክልል ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምትክ ኃላፊና የማህበራዊ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ባንታየሁ ቀፀላ በመርሃ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሀገራችን የኢኮኖሚ ምሰሶ ብቻ ሳይሆን፣ በችግር ጊዜ ለህዝብ ደራሽነቱ እና በማህበራዊ ኃላፊነት ረገድ መቼም ቢሆን የማይታማ የህዝብ ተቋም መሆኑን ዛሬም በተግባር አሳይቷል ብለዋል።


 የሀዋሳ ከተማ ምክትል ከንቲባና የንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ አጋና ኔቶ ባስተላለፉት መልዕክት የብልፅግና መንግስት ሕዝብን ማዕከል ያደረጉ ሰው ተኮር ሥራዎችን በቁርጠኝነት እየሠራ እንደሚገኝ ገልጸዋል። 


የከተማ አስተዳደሩም ለአቅመ ደካማ ዜጎች ደራሽ በመሆን ረገድ ዘርፈ ብዙና አበረታች ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን አስገንዝበው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከንግድ ሥራው ባሻገር ከማኅበረሰቡ ጋር በቅርበት ለመሥራትና ሕዝባዊ ወገንተኝነቱን ለማሳየት እያከናወናቸው ያሉትን በርካታ ሥራዎች አድንቀዋል።


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሐዋሳ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ወዬሳ ጥላሁን በበኩላቸው፣ ባንኩ ካለው የንግድ ስኬት ጎን ለጎን ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ምንጊዜም ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል። ዳይሬክተሩ አክለውም ይህ የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር ከስምንቱም ክፍለ ከተሞች የተወጣጡ 218 የሚጠጉ አቅመ ደካማ ዜጎችን ተጠቃሚ ያደረገ መሆኑን አስረድተዋል።


የዕርዳታው ተጠቃሚ የሆኑት ዜጎች በበዓል ዋዜማ በተደረገላቸው በዚህ ድጋፍ የተሰማቸውን ጥልቅ እና ወደር የሌለው ደስታ ገልጸው፣ የበዓል ዋዜማውን በደስታና በተስፋ እንዲቀበሉ ስላደረጋቸው ለባንኩ፣ ለክልሉና ለከተማ አስተዳደሩ የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።


በናርዶስ አየለ


ቀጣዮቹን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን የኤስቢሲ ቤተሰብ ይሁኑ! 


Facebook: -

https://www.facebook.com/profile.php?id=61563363361689 https://www.facebook.com/profile.php?id=100064075051944

YouTube: -

https://youtu.be/fUjnn1dQLg8?si=1bzb_8Nx8mnC-Vk5

Telegram: - https://t.me/sbcnewmedia

WhatsApp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaZ2D6NH5JLsF9xJaB



አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ