በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ ለሚሳተፉ የግል ባለሀብቶች የክልሉ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ በብልፅግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ ገለፁ።

በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ ለሚሳተፉ የግል ባለሀብቶች የክልሉ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ በብልፅግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ ገለፁ።

በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ ለሚሳተፉ የግል ባለሀብቶች የክልሉ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ በብልፅግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ ገለፁ።

***************

ሀዋሳ፣ ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም(ኤስ ቢ ሲ)


የግል ባለሀብት በሆኑት በአቶ ክብሩ ቱኬ በሀዋሳ ከተማ የተገነባው 'ባለ ስድስት ወለል 'ደራራ የንግድ ኮምፕሌክስ '' ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል ።


በህንፃው ምርቃት ወቅት በክብር እንግድነት የተገኙት በብልፅግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ ባስተላለፉት መልዕክት በክልሉ ባሁኑ ወቅት በርካታ ባለሀብቶች በተለያዩ የስራ መስኮች መሰማራታቸውን በማንሳት በዚህ ለዜጎች የስራ ዕድል እየተፈጠረ መሆኑን ጠቅሰዋል።


የኢንቨስትመንት መስፋፋት ለኢኮኖሚ መነቃቃት ከፍተኛ ሚና እንዳለው ያመለከቱት አቶ አብርሃም ለዜጎች የስራ ዕድል ከመፍጠር አንፃርም የጎላ ሚና ይጫወታሉ ብለዋል።


የክልሉ መንግሥት በክልሉ በተለያዩ ዘርፎ ለተሰማሩ የግል ባለሀብቶች አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።


ከትንሽ ስራ ተነስተው ለታላቅ ስኬት የሚበቁ ግለሰቦች በተለየ ሁኔታ ለወጣቱ ትውልድ መነቃቃትን ይፈጥራሉ ያሉት አቶ አብርሃም ስኬትን በትክክለኛው መንገድ ማሳካት ደግሞ ከሁላችንም ይጠበቃል ብለዋል።


የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ በበኩላቸው የሀዋሳ ከተማ በአሁን ሁለንተናዊ ለውጥ በማምጣት የበርካቶችን ቀልብ መሳቧን ተናግረው ለኢንቨስትመንት እና ንግድ ተመራጭ እሆነች መቀጠሏን አስረድተዋል ።


ደራራ የንግድ ኮምፕሌክስ የመሳሰሉ ህንፃዎች ግንባታቸው ተጠናቆ ወደ ስራ መግባታቸው ለከተማዋ ተጨማሪ ዕሴት ነው ።


በሀዋሳ ከተማ ለሚገኙ ኢንቨስተሮች የከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ መንገዶች ድጋፍ እያደረገ ያለ ሲሆን የግንባታ ቦታ ወስደው ወደ ስራ ያልገቡ ባለሀብቶች ግንባታዎችን አጠናቀው ወደ ስራ እንዲገቡም አሳስበዋል ።


የ''ዳራራ ኮምፕሌክስ'' ህንፃ ባለቤት አቶ ክብሩ ቱኬ የህንፃ ግንባታው የተለያዩ ምዕራፎችን አልፎ ለምረቃ በመብቃቱ መደሰታቸውን ተናግረው የንግድ ማዕከሉ በግንባታ ወቅት ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል ፈጥሮ እንደነበር በመጥቀስ ግንባታውም ከ85 ሚሊየን ብር በላይ ኢንቨስት ተደርጎበታል ብለዋል።


ዳራራ የንግድ ኮምፕሌክስ በውስጡ የሱፐርማርኬት፣የሱቅ አገልግሎት ፣የውበት ሳሎን አገልግሎት እና የሬስቶራንት እና መሰል አገልግሎት እንደሚሰጥ አቶ ክብሩ ተናግረዋል ።


ጀማል የሱፍ


ቀጣዮቹን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን የኤስቢሲ ቤተሰብ ይሁኑ! 


Facebook: -

https://www.facebook.com/profile.php?id=61563363361689 https://www.facebook.com/profile.php?id=100064075051944

YouTube: -

https://youtu.be/fUjnn1dQLg8?si=1bzb_8Nx8mnC-Vk5

Telegram: - https://t.me/sbcnewmedia

WhatsApp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaZ2D6NH5JLsF9xJaB



አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ