ጥራት ላይ ትኩረት ተደርጎ በተሠራዉ ዘርፈ ብዙ ስራ አመርቂ ዉጤት መገኘቱን የኢፌድሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና እንስቲትዩት ገለጸ።

ጥራት ላይ ትኩረት ተደርጎ በተሠራዉ ዘርፈ ብዙ ስራ አመርቂ ዉጤት መገኘቱን የኢፌድሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና እንስቲትዩት ገለጸ።

ጥራት ላይ ትኩረት ተደርጎ በተሠራዉ ዘርፈ ብዙ ስራ አመርቂ ዉጤት መገኘቱን የኢፌድሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና እንስቲትዩት ገለጸ።


***********

ሀዋሳ፣ ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም(ኤስቢሲ)


እንስቲትዩቱ የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀምና የ2019 ዓም እቅድ ዉይይት እና የቀጣዩ 10 ዓመት ስትራቴጅክ እቅድ ዉይይት መድረክ አካሂዷል።


በ2018 ዓ/ም እንደተቋሙ በ3 ጉዳዩች ላይ በትኩረት ሲሰራ የቆየ ሲሆን አሰልጣኞችንና መሪዎችን ከማብቃት አንፃር ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን ከማልማትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በትኩረት ሲሰራ ቆይቷል።


ወቅቱ የሚፈልጋቸዉን የስልጠና መስኮች ተለይተዉ በቴክኒክና ሙያ ስልጠና እንዲካተቱ የማድረግ ስራ ,በርካታ የምርምርና የተኪ ምርቶች ላይ እንዲሁም ተቋሙ በ 2018 ዓ/ም የጥራት ዓመት ብሎ ሠይሞ አጠቃላይ የተቋም ሪፎርም አድርጎ በሰራዉ ስራ ሁለንተናዊ መሻሻሎችና አመርቂ ዉጤቶች መገኘታቸውን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር(ዶ/ር)ገልጸዋል።


የስልጠና ተደራሽነት ላይ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ 40 የሚሆኑ የምርምር ስራዎችና 170 አዳዲስ እንዱስትሪዎች መመረታቸዉንና ከ2019 እስከ 2029 ዓ/ም እስትራቴጂካዊ እቅድ በመንደፍ መስኩን ለማሳደግና ለመለወጥ የታለመለት የዉይይት መድረክ ነዉም ብለዋል።


 እንደተቋም ለተገኘው ዉጤት የውስጥ ሪፎርሙ ጉልህ ሚና እንደነበረዉ የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ ለዚህም የተቋሙን ባለሙያዎቸች አቅም በማብቃት እንደተቋም በቅንጅት በተሠራ ስራ ጭምር መሆኑን አንስተዋል።


በተቋሙ የቴክኒክና አፓሬል ፋሽን ተክኖሎጂ ፋካሊት ዲን የሆኑት ወ/ሮ መረርቱ ዋቁማ የኢንዱስትሪዉን ፍላጎት ልየታ ተደርጎ 11 አዳዲስ ፕሮግራሞች ተቀርፀዉ እስከ ደረጃ 8 ስልጠናዎች እየተሠጡ እንደሚገኙ ገልጸዋል።


የማህበረሰብ አገልግሎት ተሳትፎ ዳይሬክተር አቶ ጌትነት ተሾመ

ሰልጣኞች ክህሎት መር ስልጠና ወስደዉ ወጥተዉ ስራ ፈጣሪ እንዲሆኑ በተሠራዉ ስራ እንደሀገር ዉጤታማነቱ ተረጋግጧል ብለዋል።


በመድረኩ የኢንስቲትዩቱ አመራሮችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።


ብሩክታዊት ብርሃኑ


ለሃሳብ ልዕልና 


ቀጣዮቹን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን የኤስቢሲ ቤተሰብ ይሁኑ! 


Facebook: -

https://www.facebook.com/profile.php?id=61563363361689 https://www.facebook.com/profile.php?id=100064075051944

YouTube: -

https://youtu.be/fUjnn1dQLg8?si=1bzb_8Nx8mnC-Vk5

Telegram: - https://t.me/sbcnewmedia

WhatsApp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaZ2D6NH5JLsF9xJaB



አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ