እየተጠናቀቀ ያለው ዓመት ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላይ እንደምትገኝ የሚያመላክቱ ስኬቶች የተመዘገቡበት ነው -የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
እየተጠናቀቀ በሚገኘዉ 2018 ዓ.ም ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላይ እንደምትገኝ የሚያመላክቱ ስኬቶችን የተመዘገቡበት ነው አለ የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት።
የአገልግሎቱ ሙሉ መልዕክት እንደሚከተለው ቀርቧል
አገልግሎቱ የዘንድሮ የጳጒሜን ቀናት የሚከበሩበትን ዓውድ፣ የቀናቱን ስያሜ እና መሪ መልእክት ይፋ ያደረገበትን መግለጫ ሰጥቷል፡፡
መግለጫዉን የሰጡት የአገልግሎቱ ሚኒስትር ድኤታ አቶ ከበደ ዴሲሳ “ጳጒሜን የኢትዮጵያ ማንሰራራት ወር ብሎ ለማክበር የሚያስችሉ ስኬቶች እየተጠናቀቀ ባለው ዓመት መመዝገባቸውን ገልጸዋል ፡፡
ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ቴክኖሎጂ ነክ ዓመታዊ ስኬቶችን በመግለጫቸዉ ያነሡት ሚኒስትር ድኤታዉ የጳጒሜን ቀናት በልዩ ልዩ ስያሜዎች እና ኹነቶች ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተጠናቀቁ እንደሚገኙ አመላክተዋል፡፡
አካታች፣ ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የተሳተፉበት ነፃ እና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ የተካሄደበት፣ ኅብረ ብሔራዊት ኢትዮጵያን በፅኑ መሠረት ላይ የሚያስቀምጥ አካታች እና የነበሩ ልዩነቶችን በመፍታት የጋራ ትልሞች ላይ እንዲተኮር የሚያስችል ሀገራዊ ምክክር በስኬት የተጠናቀቀበት፣ የውስጥ አንድነቷ የተጠናከረ እና የዲፕሎማሲ ዐቅሟ ያደገች ኢትዮጵያ የታየችበት ዓመት እንደነበር አቶ ከበደ በመግለጫቸዉ አመላክተዋል፡፡
ከኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች አንጻር የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ ለመፍጠር በወቅታዊ ዓለማቀፋዊ ቀውሶች ጭምር ታልፎ ስኬት የተመዘገበበት፣ የዋጋ ግሽበትን መቆጣጠር የተቻለበት፣ የዕዳ ጫና በከፍተኛ ደረጃ የቀነሰበት፣ ገቢ የመሰብሰብ ዐቅም ከ1.5 ትሪሊዮን ብር የተሻገረበት፣ የኢንዱስትሪ ምርታማነት እና የውጭ ምንዛሪ ግኝት ታሪካዊ ዕድገት ያስመዘገበበት፣ የወጪ ንግድ ገቢ ከ10.2 ቢሊዮን ዶላር የተሻገረበት፣ በአንድ ዓለማቀፍ የኢንቨስትመንት ፎረም ብቻ ከ13.2 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ የኢንቨስትመንት የመግባቢያ ሰነድ የተፈረመበት እና በአብዛኛዉ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወደ ማውጣት ደረጃ የተሸጋገሩበት፣ የግብርና ምርት እና ምርታማነት በጋ ከክረምት በግብዓት አቅርቦት ታግዞ በከፍተኛ ደረጃ የጨመረበት ስኬታማ ዓመት ነበር፡፡
የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ ያስቻሉ ከ100 በላይ የመሶብ አንድ ማእከል አገልግሎቶች የተስፋፉበት፣ የሀገረ መንግሥት ግንባታ ሂደትን በፅኑ መሠረት የሚያስቀምጥ እና ማኅበራዊ መስተጋብርን የሚያጎለብት ስኬታማ ምክክር የተደረገበት፣ የሕዝቡን የማኅበራዊ መሻቶች ለማሳካት ሰፋፊ የበጎ አድራጎት እና የመሠረተ ልማት ማስፋፋት ሥራዎች የተከወኑበት በውጤቱም ኢትዮጵያን ከተስፋ ብርሃን ወደ ሚጨበት ዕድገት ማሸጋገር የተቻለበት ዓመት እንደነበር ክቡር አቶ ከበደ በመግለጫቸዉ አመላክተዋል፡፡
በታዳሽ ኃይል አቅርቦት፣ ግዙፍ መሠረታዊ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት እና ዐዳዲስ መሠረተ ልማቶችን ወደ ግንባታ በማስገባት የተመዘገቡ ተጨባጭ ውጤቶችንም ዳስሰዋል፡፡ የዐፈር ማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ እና የቢሾፍቱ ዓለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ መጀመር ከሜጋ ፕሮጀክቶች መካከል በክቡር ሚኒስትር ድኤታዉ በአብነት ተነሥተዋል፡፡ እነዚህን ስኬቶች፣ ከተጀመሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶች እና በዕቅድ ከተያዙ ሀገራዊ ትልሞች ጋር በማስተሳሰር ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላይ መኾኗንም አመላክተዋል፡፡
የጳጒሜን ቀናት “የኢትዮጵያ ማንሰራራት” በሚል የጋራ መሪ መልእክት ይከበራሉ፡፡
ጳጉሜን 1 - የእመርታ ቀን፣
ጳጉሜን 2 - የማንሰራራት ቀን፣
ጳጉሜን 3 - የጽናት ቀን፣
ጳጉሜን 4- የኅብር ቀን እና
ጳጉሜን 5 - የነገ ቀን በሚሉ ስያሜዎች እንደ ቅደም ተከተላቸዉ በልዩ ልዩ ኹነቶች እንደሚከበሩ ያስታወቁት ሚኒስትር ድኤታዉ ለዚህም ቅድመ ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ እንደሚገኙ አስገንዝበዋል፡፡
ዜጎች በዐዲስ ዓመት ለግል ስኬቶቻቸዉ እንደሚያቅዱት ኹሉ ለኹለንተናዊ ሀገራዊ ብልጽግናም የሚጫወቱትን ሚና ታሳቢ እንዲያደርጉ፣ የመንግሥትን ፖሊሲ እና ስትራቴጂ እንዲሁም ዕቅድ ተገንዝበዉ ተሳትፏቸዉን እንዲያሳድጉ ለማነሣሣት ቀናቱ እንደሚከበሩም ገልጸዋል፡፡
የጳጒሜን ቀናቱን ስያሜ መሠረት በማድረግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ንቅናቄዎች፣ የበጎ አድራጎት እና ማዕድ ማጋራት ተግባራት፣ ነፃ ጤና ምርመራ፣ የደም ልገሳ፣ የፓናል ውይይት እና መሰል መርሐ ግብሮች እንደሚኖሩም አስታውቀዋል፡፡
#FDREGovermentCommunication
የከሸፈው የግብጽ፣ የሻዕቢያና የህወሓት ኢትዮጵያን የማዳከምና የማፍረስ ሴራ!
የክልሉ የሰላም ተምሳሌትነት ዘላቂ እንዲሆን ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው-የሲዳማ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ
19ki Gobboomu Baandiru Barra IFDR Pirezidaantich Noowa Iibbadu Amanyootinni Ayirrinsanni
ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከተመድ ምክትል ዋና ጸሐፊ ጋር ውይይት አደረጉ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሹመቶች ሰጥተዋል
የአውሮፓ ኅብረት አዲስ ለተመሠረተው የመደመር መንግሥት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፈ
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት፦
የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት
የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት፡-
ምክር ቤቱ የፌዴራል መንግሥት አስፈፃሚ አካላትን ስያሜ፣ አደረጃጀት፣ስልጣንና ተግባር ለመወሰን የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ አጸደቀ
አዲስ የተመረጡት የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤዎች የሥራ ርክክብ አደረጉ
አዲሱ የመደመር መንግሥት ዛሬ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሁለተኛ ጊዜ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ቃለ መሃላ ፈጸሙ
የአዲሱ መንግሥት ምስረታ ዛሬ ይካሄዳል
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በባሕር ዳር ከተማ ቁልፍ የልማት ቦታዎችን ጎበኙ
የኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ የኢሬፈና (ምስጋና ማቅረብ) ሥነ ሥርዓት
አቶ መምሩ ሞኬ የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ሆነው ተሾሙ
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት
Xaphoomu Ministerich Abiy Ahimed (Dr.) Keeniya Ei
የሲዳማ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የላቀ አፈፃፀም በማስመዝገቡ እውቅና ተሰጠው።
የሲዳማ ክልል ምክር ቤት 27 ዳኞችን ሹመት አፀደቀ።
ምክር ቤቱ የዋና ኦዲተር ሪፖርትን አፀደቀ ።
ለጤና ባለሙያዎች አዲስ ፍቃድና ማሳደስ፣የትምህርት ማስረጃ መስጠት እና የመድሀኒትና ምግብ ቁጥጥር ስራዎችን በጥሩ አፈጻጸም መፈጸም መቻሉን የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ጤናና ጤና ነክ ግብዓት ቁጥጥር ባለሥልጣን ገለጸ።
በመስቀል አደባባይ እየተከበረ የሚገኘው የመስቀል ደመራ በዓል ድባብ
ደመራ — የመስቀሉ ብርሃን
የሀገር ሉዓላዊነት ጥበቃ በድንበርና በአየር ክልል ብቻ የሚወሰን ሳይሆን፣ ዲጂታል ቴክኖሎጂና መረጃን በስልት መጠቀምም የዘመኑ ቁልፍ የሉዓላዊነት ጥበቃ መሆኑን የሲዳማ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ገለጸ።
የመደመር አንቀጽ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ጅቡቲ ሲደርሱ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦመር ጊሌ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ሁለቱ መሪዎች በኢትዮጵያ እና በጅቡቲ መካከል ያለውን ኢኮኖሚያዊ ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ የጋራ ፕሮጀክት ይፋ የሚሆንበትን መድረክ ይታደማሉ።
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት
አንቶኒዮ ጉቴሬዝ አፍሪካ በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት ጥሪ አቀረቡ
አዲሱ መንግሥት መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም ይመሰረታል - አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ
ሲዳማ ብሔር ከደቡብ ኢትዮጵያ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ወንድም ህዝቦች የዘመን መለወጫ በዓላትን አክብረዋል
በዝቅተኛ ኑሮ ምክንያት ለተለያዪ ችግሮች ተጋላጭ የሆኑ ዜጎች ዘላቂ መፍትሔ ለመፍጠር እየተሠራ ነዉ ፦ የፌደራል የከተሞች ምግብ ዋስትና ልማታዊ ሴፍትኔት ጸህፈት ቤት
Hawaasi Quchumi Giddo Manna Shaate Jaddo Loosse Wirri Yitino Huluullamaano Harancho Yanna Giddo Seeru Hundaanni Hossino
የሲዳማ ብሔር ተወካዮች በግፋታ
ግፋታ የአንድነትና የፍቅር በዓል በመሆኑ ለሀገራችን አንድነት መሠረት ነው -ጥላሁን ከበደ
ግፋታ የአንድነትና የፍቅር በዓል በመሆኑ ለሀገራችን አንድነት መሠረት ነው -ጥላሁን ከበደ
በህዝቦች መካከል የሚሰሩ በጎ ተግባራት አብሮነትን ያጠናክራሉ_ አስፋው ጎኔሶ
የሀዲያ ብሔር የዘመን መለወጫ “ያሆዴ” በዓል በሀዋሳ ከተማ በድምቀት ተከበረ
ተናግሮ ማድረግ ፣ ቃል ገብቶ መፈጸም !