በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ቱላ ክፍለ ከተማ ጨፌ ኮቴ ጃዌሳ እና ዳቶ ጨፌ ቀበሌ ዲኤምሲ አካባቢ የመንገድ ከፈታና ሌሎች የልማት ሥራዎችን ለማከናወን ለ731 ለልማት ተነሺዎች ምትክ ቦታ በማዘጋጀት የምክክር መድረክ ተካሂዷል።

**********

ሀዋሳ፣ ነሐሴ 20/2018 ዓ/ም (ኤስቢሲ)

በመድረኩ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ እንደገለጹት፣ በከተማዋ ለረጅም ጊዜ የልማት ጥያቄ ሆነው ለህብረተሰቡ ቅሬታ ሲፈጥሩ የቆዩ ጉዳዮችን አስተዳደሩ በገባው ቃል መሠረት እልባት እየሰጠ ነው።

በዳቶ ጨፌ ቀበሌ ዲኤምሲ አካባቢ ለልማት ተነሺዎች ምትክ ቦታ በመስጠት የመንገድ ከፈታና ሌሎች የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም ከንቲባው ገልጸዋል።

በልማት ሥራው ሂደት የራሳቸውን ጥቅም ለማስጠበቅ በተለያዩ መንገዶች የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች መኖራቸውን ጠቁመው፣ እንዲህ ዓይነት አላስፈላጊ ተግባር የሚፈጽሙ ግለሰቦችን ለመለየትና ለማጣራት ጊዜ መውሰዱን ገልጸዋል።

የራሳቸው ያልሆነን ሀብት ለማግኘት የሚሯሯጡ ግለሰቦችም ከተግባራቸው እንዲቆጠቡ ጥሪ አቅርበዋል። ቅድሚያ ለተሰጣቸው አካባቢዎች ትኩረት በመስጠት የልማት ሥራዎች በቀጣይም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

የሀዋሳ ከተማ መሬት አስተዳደርና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ አቶ ዳዊት ሌላሞ በበኩላቸው፣ መንግሥት የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄዎች በሂደት እየፈታ መሆኑን ገልጸው፣ ህብረተሰቡም የተለመደውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

በመድረኩ የተሳተፉ ነዋሪዎችም በአካባቢው እየተከናወኑ ባሉ የልማት ሥራዎች መደሰታቸውን ገልጸው፣ የዘመናት የልማት ጥያቄያቸው እልባት ማግኘቱ አስደስቶናል ብለዋል። እስከአሁን የተከናወነው አሠራር መልካም መሆኑን ጠቁመው፣ የካሳ ክፍያውም በአዋጁ መሠረት እንዲፈጸም ጠይቀዋል።

በእሌኒ ሀርቃ

ለሃሳብ ልዕልና 

ቀጣዮቹን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን የኤስቢሲ ቤተሰብ ይሁኑ! 

Facebook: -

https://www.facebook.com/profile.php?id=61563363361689 https://www.facebook.com/profile.php?id=100064075051944

YouTube: -

https://youtu.be/fUjnn1dQLg8?si=1bzb_8Nx8mnC-Vk5

Telegram: - https://t.me/sbcnewmedia

WhatsApp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaZ2D6NH5JLsF9xJaB

አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ