የሲዳማ ባህል ልማት አንዱ አካል የሆነው የአፊኒ ባህል አዳራሽ የተሻሻለ ዲዛይን ዘመኑ የደረሰበት ቴክኖሎጂ የተካተተበት የዲዛይን ክለሳ ተገምግሞ በማጽደቅ ሥራው እንዲቀጥል ተወሰነ። የአዳራሹ የተሻሻለ ዲዛይን ክለሳ በሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በተመራ መድረክ ከተገመገመ በኋላ ሥራው እንዲቀጥል ተወስኗል። በመድረኩ ርዕሰ መስተዳድሩ እንደገለፁት የአፊኒ አዳራሽ ግንባታ ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ የተላበሰ ሆኖ ባህላዊ ትውፊቱን በያዘ መልኩ እንዲጠናቀቅ ትኩረት አድርገን እየሰራን ነው ያሉ ሲሆን አዳራሹ ሲጠናቀቅ ክልሉን በኮንፍረንስ ቱሩዝም የስበት ማዕከል እንዲሆን ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልፀዋል። በመርሃ ግብሩ የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ አቶ አብርሃም ማርሻሎን ጨምሮ የክልሉ አስተባባሪ፣ የክልሉ ካቢኔ አባላትና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። መረጃው የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ነው።

የሲዳማ ባህል ልማት አንዱ አካል የሆነው የአፊኒ ባህል አዳራሽ የተሻሻለ ዲዛይን ዘመኑ የደረሰበት ቴክኖሎጂ የተካተተበት የዲዛይን ክለሳ ተገምግሞ በማጽደቅ ሥራው እንዲቀጥል ተወሰነ።
የአዳራሹ የተሻሻለ ዲዛይን ክለሳ በሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በተመራ መድረክ ከተገመገመ በኋላ ሥራው እንዲቀጥል ተወስኗል።
በመድረኩ ርዕሰ መስተዳድሩ እንደገለፁት የአፊኒ አዳራሽ ግንባታ ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ የተላበሰ ሆኖ ባህላዊ ትውፊቱን በያዘ መልኩ እንዲጠናቀቅ ትኩረት አድርገን እየሰራን ነው ያሉ ሲሆን አዳራሹ ሲጠናቀቅ ክልሉን በኮንፍረንስ ቱሩዝም የስበት ማዕከል እንዲሆን ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልፀዋል።
በመርሃ ግብሩ የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ አቶ አብርሃም ማርሻሎን ጨምሮ የክልሉ አስተባባሪ፣ የክልሉ ካቢኔ አባላትና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
መረጃው የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ነው።

አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ