"የስራ ባህላችን ተቀይሯል፣ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ እንደሚቻል በተግባር አሳይተናል" አቶ ጥራቱ በየነ።

"የስራ ባህላችን ተቀይሯል፣ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ እንደሚቻል በተግባር አሳይተናል" አቶ ጥራቱ በየነ።
"የስራ ባህላችን ተቀይሯል፣ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ እንደሚቻል በተግባር አሳይተናል" አቶ ጥራቱ በየነ።
***************
ሀዋሳ፣ ነሐሴ 18/2018 ዓ/ም (ኤስቢሲ)
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር መሰረተ ልማት መምሪያ የ2018 የበጀት አመት ማጠቃለያ እና የ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል።
የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ በመድረኩ እንደገለፁት፡ በከተማዋ የስራ ባህላችን ተቀይሯል፣ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ እንደሚቻል በተግባር አሳይተናል ሲሉ ገልፀዋል።
ሀዋሳ ስልጣኔና ዘመናዊነትን ቀድማ የጀመረች ከተማ ብትሆንም በሚፈለገው ልክ ሳይሰሩ የቀሩ የልማት ስራዎች፡ አመራሩና ህዝቡ በቁጭት እና በሙሉ ተነሳሽነት ወደ ተግባር እንዲገባ አስችለዋል ሲሉ ገልፀዋል።
የከተማ ልማት ስራው ተጀመረ እንጂ አላለቀም ያሉት ከንቲባው፡ የተሰሩ ልማቶችን በዘላቂነት በመከታተል፣ የህዝብ ሀብቶችን ከጥፋትና ከብልሽት በመጠበቅ ሀዋሳን የከተሞች ቁንጮ እንድትሆን ለማስቻል የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት ቀጣይ ስራዎች ላይ ትኩረት ማድረግ ያስፈልጋልም ብለዋል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመሰረተ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ሀላፊ ኢንጂነር ቸርነት ፍላቴ እንደተናገሩት፡ የተጠናቀቀው የበጀት አመት በከተማዋ ለረዠም ጊዜ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ሆነው የቆዮ ጉዳዮች ምላሽ ያገኙበትና የተሻለ አፈፃፀም የታየበት መሆኑን ገልፀዋል።
በመድረኩ በተጠናቀቀው በጀት አመት ስለተሰሩ የልማት ስራዎች ገለፃ ያደረጉት ኢንጂነር ቸርነት ፍላቴ፡ የአመራሮችናባለድርሻ አካላት እንዲሁም የህዝቡ የነቃ የልማት ተሳትፎ ለታየው ውጤት መሰረት መሆናቸውን አንስተዋል።
ሁሉ አቀፍና አካታች የአረንጓዴ ልማት፣ የፓርኪንግ፣ የካፌዎችና የህዝብ መፀዳጃዎች፣ የእግረኛ ናየሳይክል ትራንስፖርት፣ የመብራት ፣ውሃ እና የቴሌ ዝርጋታዎች፣ የልጆች መጫወቻዎችና የስፖርት ማዘውተሪያዎች ስፍራዎች ከተሰሩ ስራዎች ተጠቃሽ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
የሀይቅ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ፣ የሀዋሳ መግቢያ በር የማደስ ስራ፣ የልማት ተነሺ ለሆኑ ዜጎች ቤቶችን ገንብቶ የማስረከብና ሌሎች ስራዎችን
በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ የተያዙ ጅምሮች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ተብሏል።
የስማርት ሲቲ ግንባታዎች፣ የተቀናጀ የመሰረተ ልማት ስራ፣ የቤት ልማት፣ የውበትና ጥራት እንዲሁም የህብረተሰብ ተሳትፎ ስራዎች የ2019 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች መሆናቸውም ተገልጿል።
በመድረኩ በተጠናቀቀው በጀት አመት የነቃ ተሳትፎ ና የተሻለ አፈፃፀም ለነበራቸው አካላት የዕውቅና መርሀግብር የተከናወነ ሲሆን፡ ዕውቅናው የተሰጣቸው አካላትም በቀጣይ የተሻለ ስራን ለማከናወን ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልፀዋል።
በፅዮን ዮናስ
ለሃሳብ ልዕልና
ቀጣዮቹን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን የኤስቢሲ ቤተሰብ ይሁኑ!

አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ